ሀገራችን በዘር በተከፋፈለችበት ዘመን ላይ ጥቁርና ነጭ እየተባባሉ ለዓመታት ሲፋጁ የነበሩት አሜሪካኖች እንኳን የስልጣኔያቸውንና የአስተሳሰባቸውን መስፋት አሳይተዋል። ስለሆነም ሰዎች በቁመናቸው ወይም በዘራቸው ሳይሆን በባህርያቸውና በስራቸው የሚመዘኑበት እንደሆነ እንድናስተውል ይረዳናል። እኛም ከዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ተላቀን በአንድነት ሀገራችንን ለመገንባት ካለችበት ድህነት ለማውጣት በውጭ ያለነውም ዘላለም በስደት ከመኖር በሀገራችን ኮርተን በነፃነት ለመኖር የሚያነሳሳ ይመስለኛል።