ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች ስብስብ መሆኗ ይታወቃል። እነዚህ ህዝቦች ባህላቸውን ፣ አስተሳሰባቸውንና አኗኗራቸውን አንድ አድርገው ሳይለያዩ ለዘመናት እንደኖሩ ይነገራል። ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ እንደታዘብነው በህዝቦች መሀል ለሚታየው መከፋፈል ቀዳሚ ተጠያቂ የፌደራል መንግስቱ እንደሆነ ተደርጎ ይታሰባል። ይህ የምናየው መከፋፈል ሊመጣ የቻለው እውን የፌደራል መንግስት የሚባለው ርዕዮተ ዓለም (ideology) በኛ ሀገር ሊሰራ የማይችል ሰለሆነ ነው ወይስ የሀገራችን መንግስት (EPRDF) የተጠቀመበት መንገድ ትክክል ስላልሆነ ነው?