ሁለት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ፍቅረኛሞች ሆነው ለዓመታት ያህል አብረው ሲወጡ ሲገቡ ከኖሩ በኃላ ልጅቷ ታረግዛለች። ወንድየው "የራስሽ ጉዳይ ነው የማውቀው ነገር የለም" በማለት ያልተወለደው ልጅ አባትነትን አልቀበልም ይላል። ለተወሰኑ ወራት ትምህርቷን ለመከታተል ብትችልም ከሆዷ መግፋት እኩል እያየለ የመጣው የሞራል ስብራትና ተስፋ መቁረጥ ትምህርቷን እንድታቋርጥ ያስገድዳታል። በሀገራችን ህግ ለእንደዚህ ዓይነት ኃላፊነት ለጎደላቸው ወንዶች የተቀመጠ ህገ ደንብ ባይኖርም ይህንን ልጅ በፍርድ ቤት ከሳ የሞራል ካሳ ፣ ሌላም ጥቅማ ጥቅም ልታገኝ አይገባትምን?